ውይይቱ የነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርጫ ወቅት ቆይታና የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ቅበላን የተመለከቱ ጉዳዮች ተነስተውበታል፡፡
የመጪው ምርጫ ቀን ሊራዘም እንደሚችል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለፁን ተከትሎ የተማሪዎችን ቆይታ በተመለከተ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወጥ የሆነ መመሪያ መከተል ያስፈልጋል ተብሏል።
በመሆኑም በቅርቡ በበይነመረብ አማካይነት ስብሰባ በማካሄድ ግልጽ መመሪያዎች ይፋ እንደሚደረጉ ተነስቷል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም ድረስ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲቀጥሉም አቅጣጫ ተቀምጧል።
ተማሪዎች በምርጫ ወቅት የት መሆን እንዳለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በማኔጅመንት ካውንስል በመወያየት የውሳኔ ሀሳቦቻቸውን በአጭር ጊዜ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲልኩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በምርጫው ዩኒቨርሲቲዎች ከፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ በመሆን ሰላም የሚያሰፍኑ ጉዳዮችን በማንሳትና የዕውቀት ክፍተቶችን በመሙላት በሳይንሳዊ እይታ ሁኔታዎችን መተቸት እንደሚገባቸውም ተነስቷል፡፡
የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ ቋንቋዎች በተለይ በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በሱማሊኛ ውይይት በማድረግ
ምሁራን አስተዋጽዖ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።
በውይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲዎች የኮቪድ-19 መከላከል ሥራም ተዳሷል።