በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ አዲስ ለሚገነባው የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ በተገኙበት ተቀምጧል።
ለግንባታው የሚያስፈልገውን 15 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚሸፍነው የዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር ሲሆን፣ 5 ሚሊዩን ብር ወጪ የሚጠይቁ የውስጥ ቁሳቁሶቹ ደግሞ በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) እና በመንግስት የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡
ግንባታው ባለ 5 ወለል ህንፃ ያለው ሲሆን፣ በውስጡም ላብራቶሪ፣ ቤተ መፃህፍት፣ የአይሲቲ ክፍል፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ የአስተዳደር ቢሮዎችንና የመፀዳጃ ክፍሎችን ያካትታል ተብሏል፡፡
የዳሸን ቢራ ፋብሪካ ከ600 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ የተለያዩ የልማት እና የማህበረሰብ አቀፍ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የገለፁት የዳሸን ቢራ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታነህ ዝቄ፤ ፋብሪካው በከፍተኛ ግብር ከፋይነቱም የወርቅ ተሸላሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።
Via Tikvah