በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም ባሉበት እንደሚቆዩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity አሳውቋል።
የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አመለወርቅ ህዝቄል እስከዛ ባለው ጊዜ ምርጫው የሚደረግበትን ቀን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል ብለዋል።
ምርጫው በማይካሄድባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ጉዳይ ላይም በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥ ኃላፊዋ ገልፀዋል።
ትምህርት የሚጀምርበትን ወቅት ለመወሰን ወጥ የሆነ የጊዜ መርሀ ግብር ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊዋ ፤ ሚኒስቴሩ እስከ መጪው አርብ የተደረሱ ውሳኔዎችን እንደሚያሳውቅ ለቲክቫህ ገልፀዋል።