የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የንግድና መጠጥ ቤቶችን ተጽዕኖ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
ቢሮው "በመልካም ስብእና የታነፁ" ተማሪዎችን ለማፍራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል፤ በጋራ ለመስራትም ስምምነት ተፈራርሟል።
“በትምህርት ተቋማት አካባቢ የመማር ማስተማር ሂደት የሚያውኩ የንግድ፣ መጠጥ ቤቶችና መሰል ተቋማትን, ተጽዕኖ የመከላከል ስራ እየተከናወነ ነው” ሲሉ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ በመድረኩ ገልጸዋል። (ENA )