የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ትምህርት ብርሃን ምዘና መመሪያ ወደ ክልሎች ለማውረድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እያካሄደ ነው፡፡
መመሪያው ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የሚችለውን ጎልማሳ በራሱ ቋንቋ በመመዘን መለየት የሚቻልበት ስርዓት ነው።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ጌታሁን ጋረደው(ፒ ኤች ዲ) ስርዓቱ እንደ ሃይማኖት ተቋማት ያሉ ከመደበኛው ትምህርት ውጪ ትምህርትን የሚሰጡ በመኖራቸው ይህንን ለመመዘን ያስችላል ብለዋል።
ስርዓቱ ሀገር በቀል እውቀቶችን መለካት በሚያስችል መልኩ እንደሚዘረጋም ተናግረዋል፡፡
ሀገር በቀል እውቀት ያላቸው ሰዎች የትምህርት ብርሃን ምዘና ተግባራዊ ሲደረግ ማንበብ፣ መጻፍና ማስላት የሚችሉና “ እኔ መሃይም አይደለሁም ” የሚል ጎልማሳ ሁሉ በፍቃደኝነት እንዲመዘን ጥሪ ቀርቧል፡፡
በአዲሱ የትምህርት ብርሃን የምዘና ስርዓት ተመዝነው ውጤት ያመጡ ጎልማሶች ከመደበኛው የ3ኛ ክፍል ጋር አቻ ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል፡፡