በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የደምብ ልብሶቹ ውስጥ ጫማና ቦርሳ በማካተት ወደ ስርአቱ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል፡፡
ለዚህም በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትየት አማካኝነት ፣ ፕሮጀክቱን የሁለተኛ መንፈቀ አመት የትምህርት ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ወደ ተማሪዎቹ ለማስተላለፍ ርብርብ እየተደረገ ስለመሆኑ ብስራት ሰምቷል፡፡
የኢንስቲትዩት የጫማ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዙልፊካር አባጂሀድ በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ፤ በቀጣይ 2 ወራት ጫማ እና ቦርሳን በደንብ ልብሱ አልያም ዩኒፎርም ጋር በማካተት ወደ ስርአቱ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ከኬጂ ጀምሮ ፣ ከ 1 እስከ 4 እና ከ5 እስከ 8 የትምህርት ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች (አምስት መቶ ሺ) 500,000 ጥንድ ጫማዎችን እንደሚመረት ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ፕሮጀክቱን ከመቅረጽ ጀምሮ ባለድርሻ አካላትን የማወያየት ፣ የምርት ዲዛይን የመቅረጽ ፣ ፋብሪካዎች ላቀረቡት ናሙናዎች የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት እና ሌሎች ስራዎችን ያከናውናል፡፡
ከሲዳማና ከኦሮሚያ ክልሎች ጋርም ውይይት እየተደረገ ስለሆነ በቀጣይ የጋራ እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
Via- ቤተልሄም እሸቱ/ብስራት ራዲዮ