የኦሮሚያ ክልል ከአፋርና ከሲዳማ ክልል በሚዋሰንባቸው ወረዳዎች የክልሎቹን
ቋንቋዎች በትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በምስራቅና በምዕራብ ሐረርጌ በአጠቃላይ በ11 ትምህርት ቤቶች የሱማሊኛ ቋንቋ እንደተጨማሪ የቋንቋ ትምህርት መሰጠት መጀመሩን የኦሮሚያ ክልል ት/ቢሮ መግለጹ ይታወሳል።