በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የገርባ አል-ነጃሽ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ!
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የገርባ አል-ነጃሽ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።
ከአጠቃላይ የግንባታ ወጪው 7 ሚሊዮን ብር በህብረተሰቡ መዋጮ ሲሆን ቀሪውን ወጪ መንግስት ድጋፍ አድርጓል ተብሏል።
ትምህርት ቤቱ 15 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ዘንድሮ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር ታውቋል። (EBC)