↘️ ተፈታኞች የመልስ ወረቀቱን ሲሞሉ የሚፈጽሙት ስህተት ያልተጠበቀ ውጤትን ለማግኘት መንስኤ ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
↘️ ተማሪዎች መልስ የሚሰጡበት የመልስ ወረቀት የሚነበበው በቅጽ ማንበቢያ መሣሪያ ወይም ማረሚያ መሣሪያ / 0pitical Mark Reader/ ነው፡፡ ስለዚህ ተፈታኞች በፈተና ወቅት መልስ ሲሠሩ ከሳጥኖቹ ሳያልፉ አድምቀው ማጥቆር አለባቸው፡፡
↘️በደማቁ ያልጠቆሩ ወይም በከፊል ብቻ የጠቆሩ የመልስ ወረቀቶች ለማረሚያ ማሽኑ ስለማይነበቡለት ጥራቱ በተጠበቀ እርሳስ ብቻ በመጠቀም አድምቆ ማጥቆር አስፈላጊ ነው፡፡ በብዕር ወይንም በእስክርብቶ የተጠቆረ የመልስ ወረቀት ማረሚያ ማሽኑ ስለማያነበው ከእርሳስ ውጪ መጠቀም አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡
↘️የተሻሸ፣የታጠፈ በእስክርብቶ የተጠቆረ ወይም መጻፍ የተከለከለባቸው ቦታዎች ላይ የተጻፈበት የመልስ ወረቀት የማረሚያ ማሽኑ ማረም ስለማይችል የተከለከለ ነው፡፡
የመልስ ወረቀት የሚያካትታቸው መረጃዎች
✅1. የእያንዳንዱ ተፈታኝ ስም፣ የአባት ስም እና የአያት ስም በጽሑፍ የሚገለጽበት ክፍት ቦታ /ከተፈቀደው ቦታ ውጭ አለመውጣት/
✅2. የትምህርት ቤቱ ስም የሚጻፍበት ክፍት ቦታ፣ የትምህርት ቤት ይዞታ
✅3. የምዝገባ ቁጥር ተሞልቶ ቁልቁል በትይዩ ያሉ ቁጥሮች የሚጠቆሩባቸው ቦታዎች
✅4. የትምህርት ቤቱ መለያ ቁጥር ተሞልቶ ቁልቁል በትይዩ ያሉ ቁጥሮች የሚጠቆሩባቸው ቦታዎች
✅5. በእለቱ የሚወሰድ የትምህርት አይነቶች መጥቆር አለባቸው
✅6. ለእያንዳንዱ ጥያቄ በተፈታኝ የተመረጡ መልሶች የሚጠቆሩባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡