የእውቅና ፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰረዘባቸዉ የ23 ትምህርት ተቋማት ዝርዝር፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ፤ ጥራትና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለሰልጣን በትምህርት ጥራትና ሙያ ብቃት መስፈርት መሰረት ከደረጃ በታች ናቸው ያላቸውን 23 የትምህርት ተቋማትን የእውቅና ፍቃድ መሰረዙን አሰታወቀ፡፡
ባለሰልጣኑ የ2013 አመት የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት የእውቅና ፍቃድ ያገኙና ያላገኙ ተቋማትን መለየቱን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
በዚሁም መሰረት በትምህርት ጥራትና ተገቢነት ላይ የሙያ ብቃት ደረጃ ያሟሉ 574 የትምህርት ተቋማትን የሙያ ብቃትና የእውቅና ፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊከት መስጠቱን የባለሰልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ በትምህርት የሙያ ብቃት የእውቅና ፍቃድ ማረጋገጫ መስፈርት መሰረት ከደረጃ በታች ናቸው ያላቸውንና ህጋዊ ያልሆኑ 23 የትምህርት ተቋማትን የእውቅና ፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መሰረዙንም ዋና ስራ አስኪያጇ አስታውቀዋል፡፡