የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን እንዳጠናቀቀ ይሰጣል ተብሏል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ 8ኛና የ12 ክፍል ፈተናን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ አሳስበዋል።
ምንጭ:-ኢትዮ ኤፍ ኤም