በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን የትራፊክ መጨናነቅ ከማስቀረት አንፃር
ተማሪዎች መጓጓዣ ሰርቪስን እንዲጠቀሙ የሚይደርግ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።
ከፌዴራል የትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ረቂቅ መመሪያው እንዲወጣ እየተሰራ የገለፁት የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ጅሬኛ ሄርጳ ትምህርት ሲጀመር በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቅረፍ አንፃር ከፍተኛ ሚና አለው ተብሎ የቀረበ ሃሳብ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቀዋል።
Stay Safe!