ስምምነቱ ለተማሪዎች የአይሲቲ ስልጠና ለመስጠት እና ውድድር ለማካሄድ ያግዛል ተብሏል።
የቴሌኮም መሠረተ ልማት መሣሪያዎች አቅራቢ የሆነው ሁዋዌ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በአይሲቲ አካዳሚዎች አማካይነት ለ500 ተማሪዎች ስልጠና ይሰጣል ነው የተባለው።
ሁዋዌ ከኢትዮጵያ 39 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 1ሺህ ተማሪዎችን ለብሔራዊ ሽልማት ያወዳድራል ተብሎ እንደሚጠበቅም በስምምነቱ ወቅት ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ የቴሌኮም ልማት ከ20 ዓመታት በላይ የተሳተፈው ሁዋዌ፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ እድል ፈጥሯል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሁዋዌ አይሲቲ የስልጠና ማዕከል ግንቦት 24/2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መመረቁ ይታወሳል። #አዲስዘይቤ