አዲስ የሚገቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምንም አይነት የቅድመ ምዘና ፈተና እንደማይወስዱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።
የመጀመሪያ ዓመት (freshman) ትምህርታቸውን አጠናቀው የትምህርት ክፍል ምርጫ ሲያደርጉ የምዘና ፈተና ሊወስዱ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
አሁን ላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ እንደሚገቡ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመባል የተለዩት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለአመልካች ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ አድርገው የምዘና ፈተና መስጠታቸው ይታወሳል።
Via Tikvah