አዲስ በፀደቀው የዩኒቨርስቲዎች ምድብ መሰረት 8 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር፣ 15 የትምህርት ተቋማት የአፕላይድ፣ 21 የትምህርት ተቋማት አጠቃላይ እና 3 የትምህርት ተቋማት ደግሞ ስፔሻላይዝድ በሚል በአጠቃላይ 45 ዩኒቨርስቲዎች በአዲስ በምድብ ተለይተዋል።
የጥናትና ምርምር ምድብ ስር፡-
አዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ሀሮማያ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ እና መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል፡፡
የአፕላይድ ምድብ ስር፡-
አርሲ፣ አሶሳ፣ አክሱም፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮተቤ፣ ጅግጅጋ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሰመራ፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ወልቂጤ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል
አጠቃላይ ምድብ ስር፡-
ጋምቤላ፣ መቱ፣ ሚዛን፣ ዋቻሞ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል፡፡
በስፔሻላይዝ ምድብ ሥር
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተካተዋል፡፡
መማር የምትፈልጉትን ትምህርት ለማግኘት ይሄን ምድብ ማገናዘብ አለባችሁ::እዚህ ውስጥ ያልተካተቱ ዩኒቨርስቲዎች አሉ::