የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ፦
- 14 ሴት ተማሪዎች ፈተና በመውሰድ ላይ ሳሉ ወልደዋል፤14ቱ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወዳለው የጤና ተቋም ተወስደው ከወለዱ በኋላ እንዲያርፉ ተደርገው ፈተናውን ወስደዋል፡፡
- ፈተናው ያለ ፀጥታ ችግር «በተሳካ» ሁኔታ በመላው ክልል 336 የፈተና ጣቢያዎች ተሰጥቷል።
- 150,651 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደሚወስዱ ቢጠበቅም 148 ሺ 149 ተማሪዎች ማለትም 98.43 በመቶው ፈተናውን ወስደዋል።
- የኦሮሚያ ክልል ተፈታኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 36 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ።
- በፈተናው ያልተገኙ የ2,362 ተማሪዎች እጣ ፈንታ በትምህርት ሚኒስቴር ይወሰናል።