በትግራይ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አካባቢ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለ12ኛ ክፍል
ተፈታኞች ወደ ከፍተኛ ትምርት ተቋማት በሚያስገባው የማለፊያ ነጥብ ላይ አስተያየት እንደሚደረግ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ በሰጡት መግለጫ፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና በትግራይ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ በአካባቢያቸው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ስነበሩ በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ላይ አስተያየት እንደሚደረግላቸው ጠቅሰዋል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ፈተናው በሰላም መከናወኑን አመልክተዋል።
ለዚህም የመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ አስነብቧል።