በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ድጋፍ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የተገነባው የባንቆ ዳዳቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በደቡብ ክልል ከተገነቡት 3 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱን መርቀዋል።
በምርቃት ሰነ-ስረዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መሰተዳድር ርዕቱ ይርዳው፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በመጀመሪያ ዙር በሁሉም ክልሎች ካስገነባቸው 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በደ/ብ/ብ/ክ/መ ከተገነቡት 3 ትምህርት ቤቶች አንዱ የሆነውን እና በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ባንቆ ዳዳቱ ቀበሌ ያስገነባውን ትምህርት ቤት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መርቀዋል።
ጽ/ቤቱ በደ/ብ/ብ/ክ/መ ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች 30 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በሽካ ዞን ማሻ ወረዳ እና ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ይገኛሉ።
ዛሬ የተመረቀው ባንቆ ዳዳቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የቤተ ሙከራ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጻሕፍት እና የኮምፒውተር ላብራቶሪ ያካተተ ነው።
የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በደቡብ ክልል በሸካ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ያስገነባቸውን ቀሪ 2 ትምህርት ቤቶች በቅርቡ እንደሚያስመርቅም የኢቲቪ ዘገባ ያመለክታል።