ትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ
የሚቀርቡትን የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ባለሙያዎች በአውደ ጥናቱ ላይ በመሳተፍ ለረቂቅ መመሪያው ግብዕት የሚሆኑ ሃሳቦችን አንስተው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በአውደ ጥናቱ የተሳተፉት ባለሙያዎችም መመሪያው በውድድር ሂደት ልነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል::