በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ 2013 ዓ/ም በ156 መፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዛወራቸውን የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
የክልላዊ ፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች ዛሬ ተሰራጭቷል።
ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻችው መመልከት ይችላሉ ተብሏል።