ትምህርት ሚኒስቴር ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው
ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል።
በዘንድሮ አመት በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ እንደሆኑ ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ 450 ሺህ ታብሌቶች ደግሞ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡም ገልጸዋል። (ENA)