በዚህ መሰረት ተቋማቱን በአምስት የትኩረት መስኮች የተለዩ ሲሆን፥ በዚህም የምርምር፣ አጠቃላይ፣ የአፕላይድ ሳይንስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የቴክኒካል ዩኒቨርስቲዎች ተብለው ተለይተዋል።
በምርምር ዩኒቨርስቲነተ የተመደቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሀረማያ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ እና መቐለ ናቸው።
አክሱም፣ አምቦ፣ አርሲ፣ አሶሳ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ኮተቤ፣ ሰመራ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወልቂጤ፣ ወለጋ እና ወሎ ዩኒቨርስቲ የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች ተብለዋል።
አዲግራት፣ ቦንጋ፣ ቦረና፣ ቡሌ ሆራ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ድምቢ ዶሎ፣ ጋምቤላ፣ እንጅባራ፣ ጂንካ፣ ቀብሪ ደሃር፣ መዳ ወላቡ፣ መቅደላ አምባ፣ መቱ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ራያ፣ ሰላሌ፣ ዋቸሞ፣ ወራቤ እና ወልዲያ ዩኒቨትስቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች ሆነዋል።
የአዳማ ሳይንስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአዲስ እርበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት ተለይተዋል።
በቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ስር ደግሞ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተመድቧል።
ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ጥናቱ ስለመደረጉም ተነስቷል።
❗️ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከውዲሁ የዩንቨርስቲ ምርጫችሁ ላይ ይጠቅማችሗል