በአዲስ አበባ ለ2013 የትምህርት ዘመን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተገጣጣሚ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ሊገነቡ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እስካሁን 400 ሺህ ተማሪዎችን መመዝገባቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በኢትዮጵያ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በትምህርት ላይ ቢሆኑም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከ7 ወራት በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።
ይሁን እንጂ ትምህርት ቤቶችን ዘግቶ ማቆየት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ በመሆኑ አስፈላጊውን የጥንቃቄ በማድረግ ዳግም ተከፍተው ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ትምህረት ቢሮ እንዳስታወቀው በመዲናዋ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው።
የኮሮናቫይረስን የመከላከል አማራጮችን በመከተል የመማር ማስተማር ስራውን መጀመር አስፈላጊ መሆኑንም የዘርፉ ተዋንያን ይናገራሉ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው ‘‘ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ በተማሪዎች ዘንድ በወላጆች ዘንድ በመምህራን ዘንድ ትምህርት ቤት በሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ዘንድ ቤት በሚቀመጡበት ጊዜ የሚደርሰው ማህበራዊ፣የስነ-ልቦና ጫናዎች አሉ።