የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጅቱን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ዋና ዳይሬክተር ተሻለ በሬቻ ለኢፕድ እንደገለፁት፣ ዩንቨርሲቲው የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት አዘጋጀቶ ለኢፊድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲፀድቅ አቅርቧል።
በዚህም በቅርቡ ፀድቆ ዩንቨርሲቲው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምር ገልጿል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ፤ ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መቀበል የሚጀምር ሲሆን ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሚሰጥ የመግብያ ፈተናም እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።
በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ ዲግሪ እንደሚያስተምርም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። #EPA