በዚህም አራቱ ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ በ6 ፕሮግራሞች የእውቅና ፈቃድ እንደተሰጣቸው ነው የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለኢቲቪ የገለጹት።
በበይነ መረብ (ኦንላይን) ለማስተማር ፈቃድ ያገኙት ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ፣ ኢቲ ኦንላይን ኮሌጅ፣ ኤስቲ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ እና ላይትማፕ ኮሌጅ ናቸው።
ከዚህ በፊት በመንግስትም ይሁን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የበይነ መረብ (ኦንላይን) ትምህርት መመሪያ አለመኖሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ አሁን ግን መመሪያው ተግባራዊ ተደርጎ ትምህርት በበይነ መረብ እንዲጀመር አድርገናል ነው ያሉት።
ከዚህ በተጨማሪም ኤጀንሲው ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሲስተም ተበልጽጓል ያሉት ዳይሬክተሩ የ257 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ ወደ መረጃ አስተዳደር ሲስተም ገብቷል ብለዋል።
በዚህ ሂደት የ1.1 ሚሊየን የተማሪዎች እና ምሩቃን መረጃ እና 2750 ፕሮግራሞች ወደ ሥርዓቱ ገብቷል ብለዋል።