ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው የትምህርት ዘመን በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የአዲሱን ስርአተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር አስታወቋል፡፡
ሚኒስቴሩ በአሁኑ ሰዓት በስርዓተ- ትምህርት ዝግጅት ክልሎች ያሉበትን ሁኔታ እየገምገመ ይገኛል።
በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ገረመው ሁሉቃ(ዶ/ር)በመጪው ዓመት አዲሱ ስርአተ ትምህርት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ወደ ሙከራ ትግበራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ለሚካሄደው የሙከራ ትግበራ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ከየወረዳው ሁለት ትምህርት ቤቶች በናሙናነት ተመርጠው ትገበራው እንደሚካሄድ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
ከሰባተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ባሉ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ትግበራ ለማካሄድ መታቀዱን ነገር ግን እንደ የክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ እቅዱ ሊከለስ እንደሚችልም በመድረኩ ተገልጿል ፡፡
የስርአተ ትምህርት ትግበራውን ወደ ስራ ለማስገባትም በአሁኑ ጊዜ የስርዓተ ትምህርት ማእቀፍ እና የመርዓ ትምህርት ስራው ተጠናቆ የመምህራን መምሪያ እና የተማሪዎች መማሪያ መጻህፍት ዝግጅት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል ፡፡
በሚካሄደው የሙከራ ምዕራፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት እና በመቅረፍ ስርዓተ ትምህርቱ በቀጣይነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር
#edu_news