የ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ላይ የትምህርት ቤቶች የክፍያ ጋር በተገናኘ እንዴት መጨመር እንዳለባቸው መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትምህርት ቤቶች መሰጠቱን በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ጭማሪ ክፍያ ምን ምን ላይ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስቀምጥ ሲሆን በተለይ ግን ተቋሙ ትኩረት የሚያደርግበት እና የሚወስነው የምዝገባ ክፍያን ከመገደብ ጋር በተገናኘ ብቻ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
የትምህርት መመዝገቢያ የገንዘብ መጠን ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈለገው ትምህርት ቤቶች ለመመዝገቢያ ክፍያ የሚጠይቁት ገንዘብ ከፍተኛ ስለነበረ ነው ያሉት ወይዘሮ ፍቅርተ የምዝገባ ክፍያን መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የገንዘብ ምጣኔው 25 በመቶ ጭማሪ እንዲደረግበት መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
ወርሃዊ ክፍያን በተመለከተ ተቋማቸው ጣልቃ እንደማይገባ እና ስምምነቱ በትምህርት ቤቶች እና በወላጆች መካከል እንደሚሆን የተናገሩት ምክትል ስራ አስኪያጇ ትምህርት ቤቶቹ በሚያስቀምጧቸው በቂ ምክንያች እና በወላጆች በመተማመን የሚወሰን እንደሆነ ተነግረዋል፡፡