በትግራይ የሚገኙ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ!
#Ethiopia : በትግራይ ክልል የስልክ እና የኢንተርኔት መቋረጥን ተከትሎ በክልሉ የሚማሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ምንም የታወቀ ነገር ስለሌለ ወላጆች በእጅጉ ተጨንቀዋል። ወላጆች ልጆቻቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ ያልቻሉ ሲሆን የልጆቻቸው ደህንነትም እንደሚያሰጋቸው ገልፀውልናል።
የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ ሀይሎች መቀሌን እና ሌሎች አከባቢዎችን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ከተለያዩ አከባቢዎች ወደ ክልሉ ዩንቨርስቲዎች በመግባት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም። ወላጆች የሚመለከተው አካል በዚህ ጉዳይ ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንያደርግላቸው ጠይቀዋል።
*MOSHE ለወላጆች አፋጣኝ ምላሽ ቢሰጥ ጥሩ ነዉ ።
ተማሪዎች በየጊዜው የፖለቲካ እና የጥይት ሰለባ መሆን የለባቸውም!