በአራዳ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች በተማሪዎችና በመምህራን የተዘጋጁ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን በአራት ኪሎ ማለዳ ካፌ ዛሬ ተከፈተ፡፡
በመድረኩ አውደ ርዕዩ ለአራት ቀናት የሚቆይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የፈጠራ ውጤቶችን ለህብረተሰቡ ግልጽ ለማድረግና የተሻለ የልምድ ልውውጥ እንዲኖር የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ወ/ሮ የምስራች ዘውዱ የአቡነ ጎርጎሪዎስ 1ኛና 2ኛ እንዲሁም መሰናድዎ ትምህርት ቤት የፈጠራ ስራ አስተባባሪ ሲሆኑ ተማሪዎች ያላቸውን ዝንባሌ በቁሳቁስ በመደገፍ ትርፍ ጊዜያቸውን በመጠቀም እንደቻሉ ገልጸው ይህ አውደ ርዕይ መዘጋጀቱ ስራቸውን ለማሳየት እና እውቅና ለማግኘት ይጠቅማል ብለዋል፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ አበበ አውደ ርዕዮ ከመደረጉ አስቀድሞ ለፈጠራ ስራ ትኩረት አድርገው ከትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ጋር ሲሰሩ እንደቆዩ፤
በአጠቃላይ የቀረቡት የፈጠራ ስራዎች በጣም አስደናቂ እንደሆኑ፤ ተማሪዎች ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በፈጠራ ስራ እንዲታነጹ በከፍተኛ ተቋምም የተሻለ ምርምርና ጥናት እንዲያደርጉም እድል ይፈጥርላቸዋል ለሀገራቸውም አስተዋፅኦ ያበረክታሉ በማለት በቀጣይም ከሚመለከተው አካላት ጋር በመነጋገር ሰፋ ያለቦታ በማዘጋጀት ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ማለታቸዉን ከወረዳ 7 ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡