በራስ አምባ ትምህርት ቤት ከኮቪድ - 19 በሽታ የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸዉ ናሙና ከተማሪዎች እየተወሰደ መሆኑ አሀዱ ራድዮ 94.3 ዘገበ።
በራስ አምባ ትምህርት ቤት በኮቪድ 19 ያለባቸዉ 4 ተማሪዎች በመገኘታቸዉ በየክፍሉ ምርመራ መደረግ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መመህር አቶ ስንታየዉ ገለታ ተናግረዋል፡፡
አሁን ናሙና ከተወሰደላቸዉ 22 ተማሪዎች በተጨማሪ በሁለተኛዉ ዙር በነገዉ እለት ማክሰኞ ከ3 ክፍሎች ናሙና እንደሚወሰድ አስታዉቀዋል፡፡
አራቱ ተማሪዎች ኮቪድ እንዳለባቸዉ የታወቀዉ ቤተሰቦቻቸዉ ናሙና ሰጥተዉ ነዉ ተብሏል፡፡
ተማሪዎቹ ከየክፍሉ አንድ አንድ 4 በመሆናቸዉ ከሁሉም ክፍሎች ናሙና ይወሰዳል ብለዋል፡፡
የመማር ማሰተማር ሂደቱ አሁንም ቀጥሏል ያሉ ሲሆን ለመምህራን ናሙና ለመዉሰድ መታሰቡን በተመከተ ምልክት ከታየ እንደሚወሰድ እና አሁን ላይ ከተማሪዎች ብቻ ለመዉሰድ መታቀዱን አቶ ስንታየዉ ገልፀዋል።
በራስ አምባ ትምህርት ቤት መመህር የሆኑ ግለሰብ እንደተናገሩት ደግሞ በትምህርት ቤቱ እስካሁን 6 ተማሪዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል፡፡ የታወቀዉም በጠና ስለታመሙ ነዉ ብለዋል፡፡
የሚያዙ ተማሪዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በትምህርት ቤቱ አሁን እየተደረገ ያለዉ የምርመራ ቁጥር በቂ አይደለምና ትኩረት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ አሃዱ ሬድዮ 94.3