የትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሳስቧል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ፥ "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ ታብሌቶች ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።
ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን ተናግረዋል።
የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እንዳስረዱ ኢዜአ ዘግቧል።