በአዲስ አበባ ከጥቅምት 16 ጀምሮ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ እና ቀሪ መደበኛ ተማሪዎች ደግሞ ከጥቅምት 30 ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚመለሱ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛዉ ገብሩ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ የትምህርት አመቱን የስርአተ ትምህርት ምጣኔና የክፍለ ጊዜ ድልድልን አስመልክቶ እንዳብራሩት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአዲስ አበባ ዘንድሮ መማር ማስተማሩ በሁለት ፈረቃ እንደሚሰጥ እና በዚህም ከጥቅምት 30 ቡኃላ ትምህርት የሚጀምሩ ተማሪዎች በሳምንት ሶስት ቀን 24 ክፍለ ጊዜ እንዲማሩ ፕሮግራም የተያዘላቸው ሲሆን የትምህርት አገልግሎቱም በሁለት ፈረቃ ማለትም ሰኞ ፤እሮብ ፤አርብ እንዲሁም ማክሰኞ ፤ሀሙስ እና ቅዳሜ እንዲሆን መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎቸ ደግሞ ከጥቅምት 16 ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሳምንት ስድስት ቀን እንዲማሩ ፕሮግራም የተያዘላቸው መሆኑንና ትምህርቱን ሲያጠናቅቁም ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ 7ኛ ክፍል ሙሉ እና ከ8ኛ ክፍል የአንደኛ ሴሚስተርን ብቻ ያካተተ ፈተና እንደሚዘጋጅ እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ደግሞ የ11ኛ ክፍል የሁለቱም ሴሚስተር እና 12ኛ ክፍል አንደኛ ሴሚስተር የተማሩትን ትምህርት ያካተተ ፈተና እንደሚፈተኑ ተገልጻል፡፡
ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ