በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ከ5ኛ-12 ክፍል የርቀት ትምህርት ማስተግበሪያ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ፡፡
መንግስት የዜጎችን የመማር መብት ለማረጋገጥና አንድም ዜጋ ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆን መደበኛና መደበኛ ያለሆኑ ትምህርት ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ዜጎች የትምህርት እድሉ ተጠቃሚ እዲሆኑ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
========//=============//============
በመሆኑም ከነዚህ ፕሮግራሞች አንዱ የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ሲሆን ፕሮግራሙ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሲተገበር የቆየ ቢሆንም ወጥነት ባለው መልኩ በሀገር ደረጃ ለመተግባርና የትምህርት ጥራቱንም ለመከታተል በሚያመች መልኩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ከ5ኛ-12 ክፍል ረቂቅ የርቀት ትምህርት ማስተግበሪያ መመሪያ ማዘጋጀቱን ገልፃዋል፡፡
========//=============//============
ረቂቅ ማስተግበሪያ ማንዋሉ ስለ ርቀት ትምህርቱ ተጠቃሚዎች፣ የሞጁል አዘጃገጃጀት፣ማጠናከሪያ ትምህርት መስጫ ማዕከላት አደረጃጀትና ትምህርት አሰጣጥ፣ የምዘና ስርዓት ፣የተማሪዎች ምዝገባና ሪከርድ አያያዝ፣ የሚመለከታቸው አካላት ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የተቋማት የፍቃድ አሰጣጥና ስረዛን በተመለከተ በውስጡ መያዙና ከክልል በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች አንድ ዙር ውይይት የተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡
========//=============//============
ረቂቅ ሰነዱ በቀጣይም ከባለሙያዎቹና ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጎበት ሲፀድቅ ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡